M-PESA EQUB Amharic
ዕቁብ የኢትዮጵያ ባህላዊ ገንዘብ ማሰባሰቢያና የተሰበሰበው ገንዘብ በየተራ ለአባላት የሚከፋፈልበት ዘዴ ነው። ሳፋሪኮም ኤምፔሳ ሞባይል የፋይናንስ አገልግሎቶች ኃ/የተ/የግል ማኅበር (ሳፋሪኮም ኤምፔሳ) የተፈቀደለት የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ እንደመሆኑ በኤምፔሳ መተግበሪያ ሥርዓቱ ሥር ይህንን በየተራ የተሰበሰበ ገንዘብ የሚከፋፈልበትን ዘዴ ለማገዝና ለማሳለጥ የሚያስችል ዲጂታል መፍትሔ አቅርቧል።